አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፌደራል መንግሥት የተከናውኑ ዓመታዊ ሥራዎችን ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ “ዛሬ በፌደራል መንግሥት የተከናውኑ ዓመታዊ ሥራዎችን የምንገመግምበት ዕለት ነው” ብለዋል።
“ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ዕቅድ ማውጣት፣ የክንዋኔውን ሁኔታ ግብ ተኮር በሆነ፣ በቁጥር በሚለካ እና ሊመዘን በሚችል መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል” ሲሉም ገልፀዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

