Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለ2017/18 የምርት ዘመን የማዳበሪያ ግዥ ሂደት መጀመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2017/18 የምርት ዘመን 25 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ መታቀዱን እና የግዥ ሂደቱም መጀመሩን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የ2016/17 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ሥርጭት የባለድርሻ አካላት የእውቅናና ምስጋና መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው።

በ2016/17 የምርት ዘመን ከ18 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልሎች መሰራጨቱን እና ከ87 በመቶ በላይ ለአርሶአደሩ መድረሱን ሚኒስትሩ በመርሐ-ግብሩ ላይ ተናግረዋል፡፡

ወደ ሥራ የገባው አዲሱ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መመሪያም በተያዘው የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ግዥና አቅርቦት ላይ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር አስችሏል ብለዋል።

በዙፋን ካሳሁን

Exit mobile version