Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የህዳሴ ግድብ ግንባታ በ5 ዓመት ማዘግየት ኢትዮጵያን 41 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ያሳጣታል- የባለሙያዎች ግብረ ሃይል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ በአምስት ዓመት ማዘግየት ኢትዮጵያን 41 ነጥብ 7 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያሳጣት በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ግብረ ሃይል አስታወቀ።

የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ምሁራንን የያዘው ግብረ ሃይሉ ትናንት የተለያዩ የምጣኔ ሃብት ስሌት ማናወኛ መንገዶችን በመጠቀም ደረገውን ጥናት መሰረት በማድረግ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ የህዳሴግድብ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግር ትስፋ መሆኑን ጠቅሷል።

የ110 ሚሊየን ህዝብ መኖሪያ የሆነችው ሀገሪቱ በድህነት ውስጥ የሚገኙ ዜጎቿን ህይወት ለመታደግ የዚህ የሀይል ማመንጫ ግድብ ቁልፍ መሆኑን በመጠቆም የግድቡን ግንባታ ማዘግየት እንዚህን ዜጎች በድህነት ውስጥ እንዲቆዩ መፍረድ መሆኑን አስታውቋል።

ግብረ ሃይሉ በመግለጫው የግድቡ ሀይል የማመንጫ ጊዜ በተራዘመ ቁጥር ሀገሪቱ በኢንዱስትሪ ማስፋፋት ላይ የያዘችውን ግብ እንደሚያፋልስ ያስረዳል።

በተጨማሪም የግብርና ዘርፏን በማዘመን የኤልክትሪክ ሃይልን በመጠቅም መስኖን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረትንም የሚያጨናግፍ ነው ብሏል።

የግድቡ የኤልክትሪክ ሃይል የማመንጨት ተግባርን ማዘግየት ዛሬ ላይ በእንጨት ላይ የተደገፈውን በሚሊየን የሚቆጠር ዜጋ የሃይል ፍሎጎቱን በዚሁ መልኩ እንዲያሟላ በማስገደድ የደን መጨፍጨፍን በማባባስ፣ በረሃማነትን በማስፋፋት የራሱን የአባይ ወንዝን ሳይቀር ፍሰቱን መቀነስ መሆኑን በማስረዳት ከዚህ በላይ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ስጋት መፍጠር የለም ነው ያለው።

ሚሊዮናት ኢትዮጵያውያን አሁንም በእንጨት እንዲጠቀሙ ማድረግ ዜጎች ከጭስ ጋር ተያይዞ ከሚመጡ የጤና እክሎች ጋር አብረው ይቀጥሉ ማለት መሆኑንም መገንዘብ ይባል ሲል አስረድቷል።

በኤልክትሪክ ሀይል እጥረት ብቻ ሀገሪቱ የተሟላ የጤና አግልግሎት መስጠት ያልቻለችባቸውን አካባቢዎች፣ በኤሌክትሪክ ሙሉ አገልግሎት መስጠት ልቻሉ የትምህርት ተቋማት እና የትራንስፖር አውታሮች እንዳሉም አንስቷል።

Exit mobile version