Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አስተዳደሩ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚሞክሩ ሀይሎችን አይታገስም – ኢንጂነር ታከለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማንኛውም ሁኔታ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚሞክረውን ሀይል ከዚህ በኋላ በፍፁም እንደማይታገስ እና ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለፁ።

በውስጥም ሆነ በውጭ የኢትዮጵያን ጉዞ ለማደናቀፍ የሚደረገውን ሴራ መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን እያከሸፈው እንደሚገኝ በትናንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ህዝብን ከህዝብ ፤ ጎረቤትን ከጎረቤት ለማጋጨት የተደረገው ጥረት እንዲከሽፍ የከተማዋ ነዋሪዎች ላሳዩት ኢትዮጵያዊ ጨዋነትም ምስጋና አቅርበዋል።

ከዚህ በኋላ በየትኛውም መገናኛ ብዙሃን ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ የጥላቻ እና የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ስራን በህጋዊ መንገድ ለማስቆም አስተዳደሩ በትኩረት እንደሚሰራም ነው በመግለጫቸው ያነሱት።

በትናንሽ ፈተናዎች ተደናቅፈን አንወድቅም ያሉት ኢንጂነር ታከለ፤ አዲስ አበባን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ ለሚወጥኑ ሰዎች እጅ አንሰጥም ብለዋል።

በታሪኩ ለገሰ

Exit mobile version