አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሠነድነት መጠቀም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) ናቸው፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ሥርዓቶቻቸውን በማቀናጀት ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሠነድነት መጠቀም ያስችላል መባሉን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚሁ መሠረት አየር መንገዱ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመሆን ምዝገባ ከመያዝ ጀምሮ እስከ መሳፈር ድረስ ያለውን የመንገደኞች አገልግሎት ባዮ ሜትሪክ መረጃን በመጠቀም ይበልጥ ለማቀላጠፍ ይሠራል ተብሏል።