አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የ2012 ዓ.ም አፈፃፀም ላይ በአዳማ ግምገማ እያካሄዱ ነው፡፡
መድረኩ የ2012 የስራ ግምገማና የቀጣይ ጊዜ እቅድ ላይ ትኩረት የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል፡፡
እንዲሁም በመድረኩ ከለውጥ በኋላ የብልጽግና ጉዞ ጅማሮ እንዴት እየሄደ ነው የሚል እና ያገጠሙ ችግሮች ለምን እንደተፈጠሩ እና እንዴት ተፈቱ የሚሉ ጉዳዮችም ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል ነው የተባለው፡፡
በተጨማሪም ወቅታዊው የመዲናዋ የጸጥታ፣የፖለቲካ ሁኔታ፣ የኮሮና ወረርሽኝና የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ዙሪያም በጥልቀት ውይይት እንደሚደረግበት ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

