Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቃልን በተግባር መፈጸም የብልጽግና ፓርቲ ተጨባጭ መለያዎቹ ናቸው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ቃልን በተግባር መፈጸም የብልጽግና ተጨባጭ መለያዎቹ ናቸው ሲሉ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሐ ግብር በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል።

አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ የበዓሉ አላማ ፓርቲው ከምስረታው ጀምሮ እስካሁን ያደረገውን ጉዞ ለመዘከር እና ቃላችንን ለማደስ ነው ብለዋል።

ፓርቲው በርካታ ፈተናዎች ቢያጋጥሙትም እነዚህን ፈተናዎች ወደድል በመቀየር አንጸባራቂ ድል ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

የትግላችን መዳረሻ ጠንካራ ሀገረ መንግስት መገንባት ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ÷ቃልን በተግባር መፈጸም የብልጽግና ፓርቲ ተጨባጭ መለያዎች ናቸው ብለዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፍ የታሪክ እጥፋት የተመዘገበበት መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡

በሁሉም ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው÷በተገኙ ውጤቶች ሳንዘናጋ ውጤቶቻችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል “የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር መቆየቱ ይታወሳል።

Exit mobile version