Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፋና እና ዋልታ በይፋ ተዋሃዱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ እና ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት አ.ማ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ በሚል መጠሪያ በይፋ ተዋሃዱ።

የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የማብሰሪያ እና ስራ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በግራንድ ኤሊያና ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በመርሐ-ግብሩ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የሚዲያው አመራሮች የድርጅቱ ሰራተኞች፣ ተባባሪ አዘጋጆች፣ የሚዲያው አጋሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ለተመሳሳይ ዓላማ የተቋቋሙት የሚዲያ ተቋማት ውህደት አንድ ግዙፍ እና ተደራሽ ሚዲያ ለመመስረት ያለመ ነው።

ውህደቱ የፋይናንስ፣ የሰው ሃይል፣ የቴክኖሎጂና የመሰረተ ልማት አቅምን በማቀናጀት የሃብት ብክነትን ማስቀረት እንደሚያስችል ተመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም የማህበራቱ ውህደት ትርፋማነትንና ውጤታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ ሁለት የቴሌቪዥን ቻናሎች፣ ሶስት ሬዲዮ ጣቢያዎችና ሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይኖሩታል።

የውህደቱ ሒደት አስፈላጊውን ሕግና ሥርዓት ተከትሎ መፈጸሙም ተገልጿል።

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version