አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2016 ዓ.ም የምርት ዘመን በስንዴ ምርት ላይ እንደሀገር የተመዘገበውን ከፍተኛ ዕድገት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ አድርጓል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ÷ አነስተኛ ማሳ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር በማረስ 123 ሚሊየን ኩንታል ማምረታቸው ተገልጿል፡፡
እንዲሁም በመስኖ ከታረሰው 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ሄክታር መሬት 107 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል ማምረት መቻሉን ነው የጽሕፈት ቤቱ መረጃ ያመላከተው፡፡
የ2016 የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት በአጠቃላይ 230 ሚሊየን ኩንታል መድረሱንም ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡
ይህም ከ2012 የምርት ዘመን ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ማሳ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች 54 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ብቻ ማምረት መቻላቸው ተነስቷል፡፡
ዛሬ ይህ ቁጥር ትርጉም ባለው መጠን ከፍ ብሏል ያለው ጽሕፈት ቤቱ÷ ይህ እመርታ በፅኑ አመራር፣ በአስቻይ ፖሊሲዎች ብሎም ምርትን ለማሳደግ በተተገበረ ያላሰለሰ ጥረት የተገኘ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡