Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢትዮጵያ 24 ሰዓታት 561 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 544 የላብራቶሪ ምርመራ 561 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 72 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በትዊተር ገፃቸው ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 409 ሰዎች አዲስ አበባ ከተማ፣ 52 ሰዎች ጋምቤላ ክልል፣ 25 ሰዎች ኦሮሚያ ክልል፣ 16 ሰዎች ትግራይ ክልል፣ 12 ሰዎች ድሬደዋ ከተማ፣ 11 ሰዎች ደቡብ ክልል፣ 8 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 8 ሰዎች ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ 8 ሰዎች ሲዳማ ክልል፣ 6 ሰዎች አማራ ክልል፣ 3 ሰዎች ሶማሌ ክልል እንዲሁም 3 ሰዎች ከአፋር ክልል ናቸው።

ከዚህ ባለፈ የ7 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 180 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 158 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 448 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 342 ሺህ 866 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 72 ደርሷል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 5 ሺህ 448 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ180 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version