አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ7 ሺህ 264 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 760 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉንም አስታውቀዋል፡፡
ይህን ተከትሎም በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 200 ደርሷል ነው ያሉት፡፡
ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት 140 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም 5 ሺህ 785 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡
በተጨማሪም 68 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ364 ሺህ 322 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሺህ 693 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

