Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብሔራዊ መግባባት ላይ ያተኮረ ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሔራዊ መግባባት ላይ ትኩረት ያደረገ ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡

ፎረሙ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በየወሩ የሚዘጋጅ ሲሆን÷በመገናኛ ብዙሃን የዜጎች ዴሞክራሲያዊ እና ነጻ ሃሳብ የማራመድ ሒደቶች እንዲያድጉ የሚደረግበት ነው ተብሏል፡፡

በፎረሙ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ምሁራን፣ ሕግ አውጭዎች እንዲሁም ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ብሔራዊ መግባባት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምንና ብልጽግናን ለማምጣት እንዲሁም የዜጎችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማሳደግ የማይተካ ሚና እንዳለው በመድረኩ ተገልጿል፡፡

አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ÷ብሄራዊ መግባባት ለሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው÷በብሔራዊ መግባባት አስፈላጊነትና ያሉ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ ለመምከር መድረኩ መዘጋጀቱን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በፖለቲካ አመለካከታችን ይሁን አቋማችን ላይ ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ ያሉት አፈ ጉባዔው÷ይህም ጤናማና ሕገ-መንግስታዊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ በሕዝቦች የበላይነትና ተጠቃሚነት እንዲሁም ሀገራዊ ጥቅምን ማስከበር ላይ ብሔራዊ መግባባት እንዲሁም የጋራ አቋም ሊኖር ይገባል ነው ያሉት፡፡

“በማንስማማባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ጠለቅ ያለ ምክክር ማካሄድ፣ መነጋገርና መስማማት፤ ባልተስማማንባቸው ጉዳዮች ደግሞ መምከርና ሰላማዊ ንግግር ማድረግ ይኖርብናል” ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

በየሻምበል ምህረት

Exit mobile version