Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ዘመቻ መጀመሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በመርሐ ግብሩ 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ለማከናወን መታቀዱን ተመላክቷል፡፡

በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራውን በስኬት ለማከናወን 9 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ሥራ የሚከናወንባቸው ተፋሰሶች የተለዩ ሲሆን÷በመርሐ ግብሩ 9 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የሚገመት ሥራ እንደሚሰራ ይጠበቃል፡፡

Exit mobile version