አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ተሰማርተው የንግድ ሥራ ለማከናወን ማመልከቻ ያስገቡና ተመርጠው ወደ ሥራ ለሚገቡ 7 ድርጅቶች የቦታ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በዛሬው ዕለት በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ውስጥ ቦታ ተረክባችሁ ሥራ ለጀመራችሁ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ነሐሴ 2014 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ ተመርቆ ሥራ የጀመረው ነጻ የንግድ ቀጣናው በተለያዩ ተቋማት ቅንጅት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተከናውኖ የኦፕሬሽን ሥራው በመሳለጥ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡