አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ሽንሌ ከተማ በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው የቶሚ ብረት ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የመሰረት ድንጋዩን ባስቀመጡበት ወቅት÷የክልሉ መንግስት ለፋብሪካው ባለቤቶች አስፈላጊዉን ድጋፍ እና እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
የሚገነባው የብረታ ብረት ፋብሪካ ለግንባታ የሚሆን ብረቶችን በጥራት በማምረት በኩል የጎላ አስተዋፅኦ ለማበርከት እንደሚያስችል መገለፁን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡