በዚህም፣-
- ቡናን በጥራትና በስፋት ማምረት፤ በተለይ የጥሪኝ ቡና ስፔሻሊቲን ማስፋፋት፣
- ልዩ ልዩ ኦርጋኒክ የሻይ ቅጠል ዝርያዎችን በልዩ ብራንድ ጂማ ላይ ማቀነባበር፣
- የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማምረትና በመጠቀም፣ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎችን ማምረት፣ ማሸግና መላክ፣
- የከብት ወተትና ሥጋ፤ እንዲሁም የዶሮ ዕንቁላል እና ሥጋን በጥራትና በብዛት በማምረት አሽጎ መላክ፣
- ልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም ለውጭ ገበያ በሚመጥን መልኩ ማቀነባበር፣ ማሸግና መላክ፣
- ልዩ ልዩ የእንጨት ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በፋብሪካዎች በጥራት ማምረት፣
- የሸክላ ፋብሪዎችን በማስፋፋት፤ ለወለል፣ ለግርግዳ እና ለጣራ የሚያገለግሉ የግንባታ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ፣
- የጂማንና የአካባቢዋን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ጸጋዎችን በማልማትና በማስተሣሠር የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ፣
- የጂማ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅበትን ሰላሙን እና እንግዳ ተቀባይነቱን ማጽናት፣
- ጎጂ ማኅበራዊ ልማዶችን እና ደካማ የሥራ ባህልን ማሻሻል የሚሉትን አቅጣጫዎች በመከተል ጂማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።