አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ በ2ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስተኛ ቀን ውሎው የፓርቲውን ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ምርጫ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ጉባኤው 2 ሺህ 100 ተሳታፊዎች በታደሙበት በደማቅ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ባሳለፍነው አርብ በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
በጉባዔው 1 ሺህ 700 የድምፅ ተሳታፊዎች እንዲሁም የ15 ሀገራት ፓርቲዎች አመራርና ተወካዮችን ጨምሮ 400 የሀገር ውስጥና የውጭ እንግዶች በተጋባዥነት ተገኝተዋል፡፡