ብልጽግና ፓርቲ የፓርቲውን ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ምርጫ እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ በ2ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስተኛ ቀን ውሎው የፓርቲውን ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ምርጫ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ጉባኤው 2 ሺህ 100 ተሳታፊዎች በታደሙበት በደማቅ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ባሳለፍነው አርብ በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
በጉባዔው 1 ሺህ 700 የድምፅ ተሳታፊዎች እንዲሁም የ15 ሀገራት ፓርቲዎች አመራርና ተወካዮችን ጨምሮ 400 የሀገር ውስጥና የውጭ እንግዶች በተጋባዥነት ተገኝተዋል፡፡