አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት ባለፋት ስድስት ወራት 169 የዘረ-መል ምርመራ ማከናወኑን አስታውቋል፡፡
ውጤቱ የተመዘገበው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዘመናዊ የዘረ-መል ምርመራ ላብራቶሪ በማደራጀትና በዘርፉ ተገቢውን የሙያ ዕውቀት ያላቸው ባለሙያዎችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር አሰልጥኖ ወደ ሥራ በማሰማራቱ ነው ተብሏል።
ከለውጡ በፊት የዘረ-መል ምርመራ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም በሀገር ውስጥ ባለመኖሩ ናሙና ወደ ውጭ ሀገር እየተላከ በከፍተኛ ወጪ ሲመረመር የነበረ ሲሆን አሁን ላይ አገልግሎቱ በሀገር ውስጥ እንዲሰጥ ማድረግ መቻሉም ተመላክቷል፡፡
የዘረ-መል ምርመራ(ዲ ኤን ኤ) ለፍትህ ሥርዓት መረጋገጥ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነም ይገለጻል፡፡
በተለይ የሰዎችን ማንነት ለመለየት፣ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ለማረጋገጥ፣ ከተወላጅነት ጋር ስለሚነሱ ክርክሮችና ቤተሰባዊ ጉዳዮች በዘረ-መል ምርመራ የሚረጋገጡ መሆኑንም ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡