Fana: At a Speed of Life!

ፌደራል ፖሊስ 169 የዘረ-መል ምርመራ አከናወነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት ባለፋት ስድስት ወራት 169 የዘረ-መል ምርመራ ማከናወኑን አስታውቋል፡፡

ውጤቱ የተመዘገበው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዘመናዊ የዘረ-መል  ምርመራ ላብራቶሪ በማደራጀትና በዘርፉ ተገቢውን የሙያ ዕውቀት ያላቸው ባለሙያዎችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር አሰልጥኖ ወደ ሥራ በማሰማራቱ ነው ተብሏል።

ከለውጡ በፊት የዘረ-መል ምርመራ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም በሀገር ውስጥ ባለመኖሩ ናሙና ወደ ውጭ ሀገር እየተላከ በከፍተኛ ወጪ ሲመረመር የነበረ ሲሆን አሁን ላይ አገልግሎቱ በሀገር ውስጥ እንዲሰጥ ማድረግ መቻሉም ተመላክቷል፡፡

የዘረ-መል ምርመራ(ዲ ኤን ኤ) ለፍትህ ሥርዓት መረጋገጥ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነም ይገለጻል፡፡

በተለይ የሰዎችን ማንነት ለመለየት፣ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ለማረጋገጥ፣ ከተወላጅነት ጋር ስለሚነሱ ክርክሮችና ቤተሰባዊ ጉዳዮች በዘረ-መል ምርመራ የሚረጋገጡ መሆኑንም ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.