Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

46ኛው የአፍሪካ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 46ኛው የአፍሪካ ኅብረት ሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ስብሰባው “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካዊያንና ዘርዓ-አፍሪካዊያን” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በስብሰባው የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶችና የኅብረቱ ተቋማት አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)÷ በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እየተሳተፉ ነው።

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀን በሚቆየው ስብስባ በተለያዩ አህጉራዊ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍና ባለፈው ወር 49ኛው የአፍሪካ ኅብረት ቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ በተወያየባቸው አጀንዳዎች ላይ ምክክር እንደሚያደርግም ይጠበቃል።

Exit mobile version