Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአንካራ ስምምነት ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካካል በተደረሰው የአንካራ ስምምነት ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ያኮተረው የመጀመሪያው ዙር ውይይት በቱርክ ተካሂዷል፡፡

ውይይቱ የተካሄደው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) እና በሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አሊ ሞሐመድ ኦማር መካከል ነው፡፡

የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ደግሞ መድረኩን ማመቻቸታቸው ተነግሯል፡፡

ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስምምነቱን በተጨባጭ ወደ መሬት ለማውረድ እንዲሁም የጋራ ጥቅምን ለማሳካት እየተሠራ እንደሆነ በውይይታቸው ላይ አንስተዋል፡፡

እንዲሁም ቱርክ ሁለቱ ሀገራት ተቀራርበው በጋራ ጉዳዮቻቸው እንዲመክሩ ለምታደርገው ጥረት ምሥጋና ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡

በቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋባዥነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ ሞሐመድ በአንካራ ተገናኝተው ስምምነቱን መፈረማቸው ይታወሳል፡፡

Exit mobile version