Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ አደም ፋራህ በቱርኩ ኤኬ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ለ8ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የቱርኩ ኤኬ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተሳትፈዋል።

ከብልፅግና ፓርቲ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ለመስራት በቅርቡ የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመው የቱርኩ ኤኬ ፓርቲ በዛሬው እለት ጠቅላላ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው አቶ አደም ፋራህ ኤኬ ፓርቲ ከተመሰረተበት ከፈረንጆቹ 2001 ጀምሮ ሁለት አስርት ዓመታት በተሻገረው የአመራርነት ዘመን በቱርክ ያስመዘገባቸውን ዘርፈ ብዙ ስኬቶች አድንቀዋል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ እና በቱርኩ ኤኬ ፓርቲ ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውንም ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version