አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕብረ ብሔራዊነትን ይበልጥ ለማጠናከር የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ሚኒስትር አቶ ፍቃዱ ተሰማ ገለጹ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ የህዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡
አቶ ፍቃዱ ተሰማ በዚሁ ወቅት÷ሕብረ ብሔራዊ እና ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመመስረት የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
ሕብረተሰቡ በሰላም፣ በልማት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡
ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ድልን ማሳካት እንደማይቻል ጠቁመው÷ የሀገርን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የሁሉም ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
በም/ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ክልል የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷የሀገርን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በትብብር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን ለማሳካት በቅንጅት መስራት ይገባል ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡