አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሤ፣ በም/ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር) እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት ሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
የሥራ ኃላፊዎቹ የባሕር ዳር ከተማን የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።