አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ዓለም አቀፍ ኹነቶችን በመሳብ ሀገራችንን የስብሰባዎች ቀዳሚ መዳረሻ እንድትሆን ወሳኝ ሚና ይጫወታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ማዕከሉ፤ የስብሰባ፣ የኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን ዘርፍን ለማጠናከር ለምናደርገው ጥረት አንድ ተጨማሪ ዐቅም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ደረጃን እንደጠበቀ ተቋምነቱም፤ የንግድ ቱሪዝምን በማሳደግና ዓለም አቀፍ ኹነቶችን በመሳብ ሀገራችንን የስብሰባዎች ቀዳሚ መዳረሻ እንድትሆን ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

