አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ከኮንፍረንስ ቱሪዝም የሚገኘውን ገቢ ከፍ ለማድረግ እንደሚያስችል የቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ ማዕከሉ ሰፋፊ አገልግሎቶችን እንዲሠጥ ታስቦ የተገነባ ነው።
ማዕከሉ የቱሪዝም ኮንፍረንስ እንዲስፋፋ የሚኖረውን ሚና በታሰበው ልክ እንዲወጣ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም ገልፀዋል።
የኮንቬንሽን ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለያዩ የመገናኛ አማራጮች የማስተዋወቅ ተግባራት በቀጣይ እንደሚከናወኑም ጠቁመዋል፤
የአዲስ አበባን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ይበልጥ የሚያጎለብት በመሆኑ ጉልህ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል።
በሰለሞን ይታየው

