Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ 800 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና 2ኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 1 ሺህ 811 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት እንዳሉት÷ዩኒቨርሲቲው ሀገር በቀል እውቀትን በመጠቀም በተለያዩ ዘርፎች የልሕቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ ነው፡፡

ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዚዳንቱ ÷ ተመራቂዎች የቀሰሙትን ዕውቀትና ያካበቱትን ክህሎት ተጠቅመው ሀገራዊ ድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለ17ኛ ጊዜ ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 46ቱ በ2ኛ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆኑ÷ከአጠቃላይ ተመራቂዎች 527 የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ተመላክቷል።

በግርማ ነሲቡ

Exit mobile version