Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የዓድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ምስረታን አበሠሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተገኙበት በይፋ ተመስርቷል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚህ ወቅት÷ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ አክሲዮን ማህበር እንዲቋቋም ጥረት ሲደረግ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ በቀጥታ ወደ ሥራ በመግባት አክሲዮን ማህበሩ መመስረቱን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ወታደራዊ አክሲዮን ማህበር የተቋሙን የፋይናንስ ዘርፍ ለማሣደግ የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ የሠራዊቱን ፋይናንሻል ተጠቃሚነት እንደሚያጠናክር አንስተዋል፡፡

ቅርንጫፎችን በማብዛት በሁሉም ቦታ ተደራሽና ፈጣን አገልግሎት ሠጪ ለመሆን መሥራት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የመከላከያ ፋውንዴሽን ሪፎርሙን ተከትሎ እንደ አዲስ ከተደራጀ ወዲህ በበርካታ ዘርፎች ለሠራዊቱ የማህበራዊ ዋስትና ሆኖ እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከፍተኛ የአክሲዮን ግዥ የፈፀሙ ዕዞች፣ ኮሮችና ዋና መምሪያዎች የተዘጋጀላቸውን የዋንጫ ሽልማትና ሠርተ-ፊኬት ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መቀበላቸውንም የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version