Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ እንደሚጀመር ምክር ቤቱ ገለጸ።
 
የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በላከው መግለጫ÷ ምክር ቤቱ ጉባኤው ከነገ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ መሆኑን አስታውቋል።
 
በቆይታውም በ2012 በጀት ዓመት የክልሉ መንግስት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የ2013 ስራ ዘመን ዕቅድና ማስፈጸሚያ በጀት ላይ በመወያየት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
 
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በተጓደሉ ካቢኔዎች ምትክ አዲስ አመራሮችን እንደሚሾም መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version