Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዓሉን ስናከብር የታረዙትን እያለበስን፤ የተራቡትን እያበላን፤ የተጠሙትን እያጠጣን ሊሆን ይገባል – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓሉን ስናከብር የታረዙትን እያለበስን፤ የተራቡትን እያበላን፤ የተጠሙትን እያጠጣን ሊሆን ይገባል ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ አስገነዘቡ።

አቶ አደም ፋራህ የትንሳዔ በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

በዓሉን ስናከብር ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን እያሰብን፤ የታረዙትን እያለበስን፤ የተራቡትን እያበላን፤ የተጠሙትን እያጠጣን ፍጹም ሰብዓዊነትን በተላበሰ ኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና ሊሆን ይገባል ሲሉም ገልጸዋል።

በተለይም የፓርቲያችን አመራር፣ አባላት እና ደጋፊዎች በዓሉ በፓርቲያችን የሰው ተኮርነት እና የሰብዓዊነት መርሆች ደምቆ እንዲከበር እያደረጋችሁ የምትገኙትን እንቅስቃሴ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ሲሉ ጠይቀው፤ በዓሉ ፍቅር፣ ደስታን እና ሰላምን በጋራ የምንቋደስበት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።

Exit mobile version