አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መርሐ ግብር ስሑል ሽረ እና ወላይታ ድቻ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሠዓት በተካሄደው ጨዋታ ፀጋዬ ብርሃኑ ለወላይታ ድቻ እንዲሁም ብርሃኑ አዳሙ ለስሑል ሽረ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል አመሻሽ 12 ሠዓት ላይ አዳማ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ይጫወታል።