Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሩሲያ የድል በዓል ላይ ለመታደም ሞስኮ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በነገው ዕለት በሚከበረው 80ኛው የሩሲያ የድል በዓል ላይ ለመታደም ዛሬ ማለዳ ሞስኮ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ ሞስኮ ሲደርሱ በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ አናቶሊ ባሽኪን አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃቱን ተከትሎ በተለይም ደግሞ የቀድሞው ሶቪየት ኅብረት በናዚ ላይ የተቀዳጀውን ድል በማሰብ በሚከበረው በዓል ላይ በርካታ የዓለም መሪዎች እንደሚታደሙ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከበዓሉ አከባበር ጎን ለጎን ከተለያዩ አካላት ጋር የሁለትዮሽ እንዲሁም ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version