አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ አርሰናል ኒውካስል ዩናይትድን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ምሽት 12:30 በሚደረገው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፏቸውን ለማረጋገጥ ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ቀን 10:15 ለሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ በሚደረገው ፉክክር ውስጥ የሚገኘው ኖቲንግሃም ፎረስት ከሜዳው ውጭ ዌስትሃም ዩናይትድን ይገጥማል።
ኤቨርተን ከሳውዛምፕተን 8 ሰዓት እንዲሁም ሌስተር ሲቲ ከኢፕስዊች ታውን፣ ብሬንትፎርድ ከፉልሃም በተመሳሳይ 11 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።