Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለ2017 የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ7 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ችግኝ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017 የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ7 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

አረንጓዴ አሻራ የተጎዳ መሬት እንዲያገግም፣ የመሬት እርጥበታማነት እንዲጨምር፣ የውሃ አካላት መጠን እንዲጨምር ማድረጉን በሚኒስቴሩ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ ፋኖሴ መኮንን ገልዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ 40 በመቶ የደንና 60 በመቶ የፍራፍሬ፣ የእንስሳት መኖ፣ የአፈር ለምነትና ጤንነትን የሚጠብቁ ችግኞችን በመትከል ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሚተከሉ ችግኞች የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት በጎርፍ አደጋ እንዳይጠቁ የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version