Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋገጠች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት ከኢትዮዽያ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የተሳሰረ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ፤ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቤንጃሚን ቦልሜል ጋር ተወያይተዋል።

የልዑካን ቡድኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከ መልዕክት አድርሷል፡፡

በዚሁ ወቅትም የደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት ከኢትዮዽያ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የተሳሰረ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን  ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ  ልዑኩ አረጋግጧል፡፡

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንትና ምክትላቸውም ኢትዮጵያ ከቀድሞ ጀምሮ እስከ አሁን የዘለቀና የማይናወጥ ድጋፍ እያደረገች መቆየቷን ጠቅሰው ለዚህም ምስጋናና አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይሄው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ትናንት ወደ ደቡብ ሱዳን በማቅናት የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕክት በማድረስ ውይይት ያደረጉት የልዑኩ አባላት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡

Exit mobile version