Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአረፋ በዓልን ስናከብር የእምነቱን አስተምሮ በመከተልና በመተግበር ሊሆን ይገባል – ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የአረፋ በዓልን ስናከብር የእምነቱን አስተምሮ በመከተልና በመተግበር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የ1 ሺህ 446ኛውን የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ሕዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር የእምነቱን አስተምሮ በመከተልና በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

ነቢዩ መሐመድ በአስተምሯቸው የአረፋ ቀን ከሁሉ የላቀች ናት ማለታቸውን አውስተው÷ በአረፋ ተራሮች መቆም ያልቻልን አማኞች ባሉበት ዱዓ በማድረግ መልካሙን በመመኘት ጭምር ልናሳልፍ ይገባል ብለዋል።

በዓሉን በቤትም ሆነ በአደባባዮች በእስላማዊ ሥነምግባር ልናከብረው ይገባልም ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

ፕሬዚዳንቱ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) ከነገ በስቲያ አርብ የሚከበር መሆኑን ገልጸው÷ በአንድነት፣ በመረዳዳትና የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመራኦል ከድር

Exit mobile version