Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መቐለ 70 እንደርታ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ቀን 9 ሠዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቤንጃሚን ኮቴ የመቐለ 70 እንደርታ ማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።

ረፋድ 3 ሠዓት በተካሄደው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ስሑል ሽረን 5 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የዕለቱ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሠዓት ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ይገናኛሉ።

Exit mobile version