Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከስሎቬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከስሎቬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ናታሻ ፒሪክ ሙሳር ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያን እየጎበኙ ያሉትንና በስሎቬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የሆኑትን ናታሻ ፒሪክ ሙሳርን በጽሕፈት ቤቴ ተቀብዬ በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።

Exit mobile version