Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከናይጄሪያዊው ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናይጄሪያዊው ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ዛሬ ወንድሜን አሊኮ ዳንጎቴን ተቀብዬ አነጋግሬያለሁ ብለዋል።

በውይይታቸውም ለኢትዮጵያ ወሳኝ የሆኑ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያስችሉ ስልታዊ የኢንቨስትመን መስኮች ላይ መክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version