አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሚያደርጓቸው ውይይቶች አካል ሲሆን፥ የንግዱን ዘርፍ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ውይይቱ በፌዴራል ደረጃ ከመደረጉ በፊት በዞን፣ በክልልና ከተሞች ደረጃ ከተካሄዱ ውይይቶች የቀጠለ ሲሆን፥ የሚመለከታቸው የሥራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተወያዮች ለመንግስት የዘርፍ እቅዶች ግብዓት እንዲሰጡ ተደርጓል።
የተደረገው ውይይት ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ጀምሮ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ይቀርባል፡፡