Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኬኛ ቤቨሬጅስ ኩባንያን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዛሬው ዕለት የኬኛ ቤቨሬጅስ ኩባንያን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ ከ22 ቢሊየን ብር በላይ ኢንቨስት ተደርጎ በ110 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውን የኬኛ ቤቬሬጅስ ኩባንያ ግንባታ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በዓመት ከ3 ሚሊየን ሄክቶ ሊትር በላይ ማምረት የሚችለው ኩባንያው፤ በቴክኖሎጂ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚችል ተገልጿል።

በአክሲዮን ማህበር የተመሰረተው ኩባንያው ከ4 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ባለ አክሲዮኖች፣ የህብረት ሥራ ማህበራትና ድርጅቶች በአንድ በመጣመር የሀገርን አቅም ያሳየ ሀገር በቀል ኩባንያ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፤ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ለ1 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተጠቁሟል፡፡

በማርታ ጌታቸው

 

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

 

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version