Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ህዳሴ ግድቡ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የቀጣናው ሀገራት ሀብት ነው – ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የቀጣናው ሀገራት ሀብት ነው አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)።

“ቀጣናዊ የኃይል ትስስር ለአካታች እና ዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ሀሳብ አራተኛው አፍሪራን ቀጣናዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምሁራን እና ሌሎች ባለድርሻዎች ተገኝተዋል።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በመድረኩ እንደተናገሩት፤ ኮንፈረንሱ ሀሳብን ወደ ተግባር ለመቀየር እና ቀጣናዊ የኃይል ትብብሮችን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና አለው።

ነፃ የንግድ ቀጣና እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ የመሰረተ ልማት ትብብር የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና የተባበሩት መንግስታት 2030 ግቦች አካል መሆናቸውን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ለግቦቹ መሳካት ትርጉም ያለውን አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል።

የታዳሽ ኃይል ልማት ሥራዎች ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ የኃይል ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውን በመጥቀስ፤ ለአብነትም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አንስተዋል።

የህዳሴ ግድቡ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የቀጣናው ጭምር ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ከግድቡ የሚመነጨው ኃይል የቀጣናው ሀገራትን የኃይል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች እንደሆነ ጠቅሰው፤ ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ኃይል እና ሌሎች መሰረት ልማቶች ማስተሳሰር አስፈላጊ በመሆኑ ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ትብብር ያልተቆጠበ ድጋፏን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን አስታውቀዋል።

በሚኪያስ አየለ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version