Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ክፍተቶችን እየሞላን የሕዝብ አገልግሎቶችን እያዳረስን እንገኛለን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት የለውጥ ዓመታት ታሪካዊ ጉድለቶችን እና ክፍተቶችን እየሞላን የሕዝብ አገልግሎቶችን ወደ ሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት እያዳረስን እንገኛለን አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

10ኛው የአፍሪካ የሲቪል ሰርቪስ ቀን እና የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጉዳዮች ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፥ የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመንግስት እና ሕዝብ መካከል ቀዳሚ የመተማመኛ መስመሮች ናቸው፡፡

የሕዝብ አገልግሎቶችን የማዳረስ ሥራ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪነትን የምናረጋግጥበት እና የአገልግሎት ማዕቀፍን ተግባራዊነት የምናሳይበት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የሲቪል ሰርቪስ እና አስተዳደር ሪፎርም መጀመሩን አንስተዋል፡፡

ሪፎርሙ በሰባት ምሰሶዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመጠቆም አዲስ እና ልዩ ተቋማዊ መዋቅር እየተገነባ ነው ብለዋል፡፡

አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ በአዲስ መልኩ ቅርጽ የማስያዝ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ያነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ በውድድር የሚመራ የአገልግሎት ማዕቀፍም ተግባራዊ እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎትን ለማዘመን የጀመርነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመዋቅርም በላይ ነው ብለዋል በንግግራቸው።

በዚህ ጉባኤ ኢትዮጵያ ልምዷን ታካፍላለች፤ ከሌሎች አፍሪካውያን ትማራለችም ብለዋል፡፡

በለይኩን ዓለም

 

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version