Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባየርን ሙኒክ ከዓለም ክለቦች ዋንጫ ተሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ክለቦች ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ የፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጂ የጀርመኑን ባየርን ሙኒክ 2 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል፡፡
የፒ ኤስ ጂን የማሸነፊያ ግቦች ዴዚሬ ዱዌ እና ኦስማን ዴምቤሌ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
ፒ ኤስ ጂ በግማሽ ፍጻሜው ከሪያል ማድሪድ እና ቦሩሺያ ዶርትመንድ አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡
ምሽት 5 ሰዓት ላይ ሪያል ማድሪድ ከቦሩሺያ ዶርትመንድ ለግማሽ ፍጻሜው ለማለፍ ይፋለማሉ፡፡
የእንግሊዙ ቼልሲና የብራዚሉ ፍሉሚኒንሴ ቀደም ሲል ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡
በአቤል ንዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Exit mobile version