አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሃሳብ ተነስቶ ለዓለም አቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደ መሆን ተሸጋግሯል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሪዮ ዲ ጄኒሮ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የብሪክስ ጉባዔ የሰላም፣ የጸጥታ እና ዓለም አቀፍ አመራር መድረክ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
በንግግራቸውም ስኬታማ ትብብርን ለማስቻል አጸፋዊ መተማመንን የሚያሳድጉ ዓለም አቀፍ ተቋማት የመኖርን አጣዳፊነት አንስተዋል።
ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የጋራ ደኅንነትን እና ሁሉን አካታች ብልጽግናን ለማምጣት ይረዳ ዘንድ የውሳኔ አሰጣጥ መዋቅራቸው ምሉዕነት ባለው መልክ የሚሻሻልበትን ሁኔታም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ በይፋ ወደ ብሪክስ የተቀላቀለችው በ2015 ዓ.ም ሲሆን÷ ኢኮኖሚያዊ ወዳጅነት ብቻ ሳይሆን ፍትኃዊ የሆነ እኩልነት የሚሰፍንበት ብዝኃ ዋልታዊ ዓለምን ለመፍጠር ከሚተጉ ሀገራት ጋር በእኩል ደረጃ የተሰለፈችበት ስብስብ ነው።
እንደ ብሪክስ አባልነቷ ኢትዮጵያ እነዚህ ጥረቶች እንዲሳኩ በተለይም በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ መድረኮች ለአዳዲስ ገበያዎች እና በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ሰፋ ያለ ውክልና በሚገኝበት ሁኔታ ላይ በንቃት አስተዋፅኦ እንደምታደርግ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የብሪክስን እያደገ የመጣ ተፅዕኖ ”ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለዓለም አቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደ መሆን ተሸጋግሯል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
“አዳዲስ አባላት በመጨመራቸውም የጋራ ድምጻችን የበለጠ ይጠናከራል፤ የጋራ አላማችን የበለጠ ይጠራል፤አቅማችንም ይሰፋልም” ነው ያሉት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!