አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት ከተረጂነት ለመውጣት የተከናወኑ ሥራዎች የኢትዮጵያን የተረጂነት ታሪክ ለመቀየር መሰረት የጣሉ ናቸው አሉ የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፡፡
የ2017 በጀት ዓመት የፓርቲው ሥራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
አቶ አደም ፋራህ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ÷ 2017 በጀት ዓመት በርካታ ሥራዎች የተከናወኑበት፣ የትጋት እና የስኬት ዓመት እንደነበር አንስተዋል፡፡
ፓርቲውን በሰብዓዊና በቁሳዊ ሃብት ለማጠናከር፣ በዘመናዊ መረጃ ለማደራጀት እንዲሁም ገዢ ትርክትና ቅቡልነትን ከማረጋገጥ አንጻር የተከናወኑ ሥራዎች ስኬታማ ናቸው ብለዋል።
በአስተሳሰብ፣ በአደረጃጀትና በአሰራር የተዋሃደ ፓርቲ ለመፍጠር የተሰሩ ሥራዎች ስኬታማ እንደነበሩ ጠቁመው÷ በዚህም የፓርቲውን 2ኛ መደበኛ ጉባዔና 5ኛ ዓመት ምስረታ በዓል በተቀናጀ መንገድ ማክበር ተችሏል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለው እንዲሆን በትኩረት መሰራቱን የተናገሩት አቶ አደም÷ በዚህም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አመልክተዋል፡፡
በንቅናቄ የተከናወኑ ሥራዎች ውጤታማ እንደነበሩ እና ሕዝቡ አካታች ሀገራዊ ምክክር ላይ እንዲሳተፍ በመደረጉ የምክክር ሒደት በተሳካ መንገድ መቀጠሉን አስገንዝበዋል፡፡
ገዢ ትርክትና ቅቡልነት እንዲረጋገጥ በተከናወነው ሥራ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ አዎንታዊ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ድሎችን ማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በመቅረፍ ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ ሕዝቡን በማሳተፍ መስራት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

