አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2018 በጀት ዓመት የማንሰራራት ጉዟችንን የሚያፀኑ አዳዲስ እመርታዎችን ለማስመዝገብ በጋራ የምንተጋበት ዓመት ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን እንደመነሻ በመውሰድ በተዘጋጀው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከፌደራል ተቋማት አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷የ2017 በጀት ዓመት በብዙ መልኩ የኢትዮጵያ የብልጽግና ታሪክ እጥፋት ነው፤ዓመቱ እውነትም የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን መነሻ የሆነ ዓመት ነበር ብለዋል።
የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድም እነዚህን መልካም አፈጻጸሞች መነሻ የሚያደርግ መሆኑን ነው ያብራሩት፡፡
በበጀት ዓመቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በማድረግ የከረሙ ስብራቶቻችንን ጠግነናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በዚህም የሕዳሴ ግድብን አጠናቅቀናል፤ የጋዝ ፕሮጀክታችንንም እያጠናቀቅን እንገኛለን፤በከተሞቻችን የጀመርናቸው የኮሪደር ልማቶች ውጤት ማምጣት ጀምረዋል፤ የገጠር ኮሪደርንም ጀምረናል ነው ያሉት፡፡
የ2018 በጀት ዓመት ግቦቻችንም እነዚህን መልካም አፈጻጸሞች መነሻ የሚያደርጉ፣ ካለፈው በላይ ትጋት እና ጥረት የሚጠይቁ ናቸው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ለብቻ መሮጥን ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ቅንጅትንም ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዛሬ በእኛ እጅ ናት፤በአዲሱ በጀት ዓመት የላቁ ድሎችን በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ማንሠራራት የሚያውጀው ትውልድ አካል እንደሆንን በማመን ለበለጠ ስኬት በትጋት መስራት ይኖርብናል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!