Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፖሊስ አገልግሎትን በማዘመን ተልዕኮን በብቃት መወጣት የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የፖሊስ አገልግሎትን በማዘመን ተልዕኮን በብቃት መወጣት የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው አሉ።

ኮሚሽኑ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከዱባይ ፖሊስ ለእጀባ እና ፈጣን መንገድ ትራፊክ ደንብን ለማስከበር የሚያገለግሉ ዘመናዊ የሞተር ሳይክሎችን ተረክቧል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንዳሉት፤ ኮሚሽኑ ከለውጡ ወዲህ በብዙ መንገድ ራሱን እያዘመነ ነው።

በዛሬው ዕለትም ይህንን ማገዝ የሚያስችል ለእጀባ እና ፈጣን መንገድ ትራፊክ ደንብን ለማስከበር የሚያገለግሉ ዘመናዊ ሞተር ሳይክሎችን በድጋፍ መልክ ተረክቧል ነው ያሉት።

በቅርቡ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች፣ አካባቢን ለመቃኘት እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ድሮኖች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን መጥቀሳቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

በዚህም የፖሊስን አገልግልትን ለማዘመን የሚያስችሉ አቅሞች እየተፈጠሩ እንደሆነ ገልጸው፤ አገልግሎቱን የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ዘመናዊ ሞተር ሳይክሎቹ ነገ የሚጀመረውን ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የስርዓተ ምግብ ጉባኤን ጨምሮ ለሌሎች ዓለም አቀፍ መድረኮች ለሚመጡ እንግዶች እጀባና የደህንነት ሥራ አገልግሎት እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version