አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ በ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደህና መጡ እላለሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሁለቱ ሀገሮቻችን በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት የሚካሄደውን 2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓቶች ጉባኤ በጋራ በመሆን አዘጋጅተዋል ብለዋል።